የሩሲያን ቋንቋ ትምህርት በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያው ዩልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጳጉሜ 5/2015ዓ.ም የሩሲያን ቋንቋ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ የአማርኛን ቋንቋ በዩልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት፤ የሁለቱ ሀገራት የባህል ለባህል ልውውጥ ስምምነት፤ የምርምር፣ የማኅበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ለመስራት፤ የሁሉቱም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችና መምህራን በጋራ ፕሮጀክት ትምህርታዊ ጉዞ፤ በጋራ ኮንፈረንስና ሲሚናሮችን ማዘጋጀት ወዘተ ስምምነት መሠረት ለ6 ወራት የሩሲያኛ ቋንቋን ሲከታተሉ የቆዩ የመጀመሪያ ዙር የ16 በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ግንቦት 22/2016ዓ.ም የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት፣ ምክትል ፕሬዘዳንቶች፣የትምህርት ዳይሬክተሮች በተገኙበት፣ የዩልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት/ሬክተር ዶ/ር ኢግኖር ኦሌጎቪች ና ሌሎች የዩልያኖቭስክ ዪኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የተከበሩ አሌክሳንደር አሌክሳንድሮቪች የሩሲያ ኢምባሲ በኢትዮጽያ አማካሪና የሩሲያ የባህልና የሳይንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ዳይሬክተር በተገኙበት ተመርቀዋል። ተመራቂዎቹ በዋናነት የሩሲያኛ ቋንቋ ማንበብና መጻፍ በደንብ ችለዋል። በዕለቱ ከተመራቂዎች 5 ተማሪዎች በሩሲያኛ ቋንቋ ግጥም አቅርበዋል። በስምምነቱ መሠረት መርሃ ግብሩ በዩኒቨርሲቲያችን የአለቃ ገብረ ሐና ባህል ጥናትና ልማት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በቀጣይ የአማርኛ ቋንቋን በዩልያኖቭስክ የኒቨርሲቲ ለማስጀመርና የሩሲያኛ ቋንቋም በዩኒቨርሲቲያችን ለተማሪዎችም ለመምህራንም መሰጠት የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።