ለደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ የአንደኛ ዓመትና ሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ
1. በባለፈው ዓመት የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ፣
2. በአዲስ አንደኛ ዓመት የተመደባችሁ እና
3. በዚህ ዓመት የሪሚዲያል ፕሮግራም እንድትከታተሉ ደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች፤
የ2016 ዓ.ም ትምህርት ምዝገባ ከየካቲት 25 እስከ የካቲት 27/2016 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
➢ በመቅደላ አምባ ዩንቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል በዚህ ዓመት ተመድባችሁ የነበረ የስማችሁ አልፋቤት ከE-K የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም ወደ ደብረታቦር ዩንቨርሲቲ ስለተመደባችሁ ይህ ጥሪ ይመለከታችኋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች
➢ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ኦሪጅናልና ኮፒ
➢ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክብሪት ኦሪጅናልና ኮፒ
➢ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሰርትፍኬት ኦሪጅናልና ኮፒ
➢ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሲሆኑ
እንዲሁም ብርድ ልብስ ፡ አንሶላ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መግባት አይቻልም፡፡
ደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት