የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 1ሺ 202 ተማሪዎችን አስመረቀ።
ሃምሌ 13/2015 ዓ.ም በመደበኛና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር እንዲሁም በክረምትና በኤክስቴሽን 1ሺ 202 ተማሪዎችን ለ10ኛ ጊዜ አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ.ም ስራ የጀመረና ቀደም ሲል በትምህርት ክፍልና ፍኩሊቲ ይጠቀሱ የነበሩትን ወደ ትምህርት ቤትና ኮሌጅ አሳድጎ በአሁኑ ሰዓት በ5 ኮሌጆችና በ1 ኢንስቲትዩቱ እና ሁለት ትምህርት ቤቶች የተዋቀረ ነው።
የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው “የዛሬዎቹ ተመራቂዎች ለየት የሚያደርጋችሁ በዩኒቨርስቲው ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የመውጫ ፈተና ሚዛን ተመዝናችሁ ለመመረቅ መብቃታችሁ ነው “የዕለቱ ተመራቂዎች የቀጣዩን ዘመን መልካም የህይወት ምዕራፍ እንዲሆንላቸው እመኛለሁ” ብለዋል
የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ሳሌ አያሌው የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር “እናንተ ተማሪዎች ሙሉ አቅማችሁንና ትኩረታችሁን አላማ ላይ በማድረግ ለዚህ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።
ከሂሳብ ትምህርት ክፍል ተማሪ አወቀ ቢያዝን በላይ 3.97 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።