
የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አከናወነ
——————————————————————————————————————————–
የደብረ ታቦር ዪኒቨርሲቲ ከደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተከናወነ ሲሆን የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ፀጉር-አዲኮ ቀበሌ ቡርሳ ተራራ የተከናወነ ሲሆን ሶስቱን ክፍለ ከተሞች ጨምሮ ከ80 ሺ በላይ ችግኞች ተተከለዋል። በችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ሰራተኞች፣ ተማሪወች፣የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ በጎ-ፈቃደኛ ወጣቶች፣ የቀበሌው አርሶ አደሮች እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ታደሰ ዋለልኝ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተገኝተው እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራዎች በተጨማሪ ለአካባቢው ማ/ሰብ በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። ከነዚህም መካከል የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው ማ/ሰብ ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተሳትፎዎቸን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተለይም የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ እና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተናግረው ይህንን ተግባር በዋናነት ለማጠናከር ዩኒቨርሰቲው የራሱን ችግኝ ጣቢያ በማቋቋም ከ260 ሺህ በላይ የሀገር-በቀል እና የውጭ ሀገር ዝርያ ያላቸው የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በማፍላት በክረምት ወራት ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደተሰሩ አመላክተዋል፡፡


