
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማእከል ከደብረ ታቦር አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ጋር በጋራ በመሆን በህክምና ላይ ከሚገኙ የስነ-አዕምሮ ታካሚወች ጋር የትንሣኤ በዓልን አከበረ።
በ2012 ዓ.ም የተመሰረተው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማእከል በሀገሪቱ ከሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ማእከላት አንዱ ሲሆን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ ታካሚወች ህክምና እና ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።
በምዕራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማ የሚገኘው የደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርኤል እና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አገልጋይ አባቶች እና አባላት ወንድም እና እህቶች በደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ የሱስ ህክምና ማዕከል እና በደብረ ታቦር አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ለሚታከሙ የስነ-አዕምሮ ታካሚወች ለባዕል መዋያ እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል ከ338,180.00 ETB ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል። ለተደረገው ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው እና በታካሚወች ስም ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
ከምስረታው ጀምሮ ለማእከሉ ውጤታማነት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ለሚሰሩ አካላት ሁሉ አድናቆትና ምስጋና እያቀረብን ወደፊትም ለተሻለ አገልግሎትና ውጤት በጋራ እንስራ በማለት ማእከሉ ጥሪውን ያቀርባል።