የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የ1445ኛውን የዒድ አል_ፈጥር ረመዳን በዓልን በጋራ አከበሩ።
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እስልምና እምነት ተከታይ ተማሪወች በተማሪወች አገልግሎት ዳይሬክተር ጽ/ቤት እና በተማሪወች ህብረት አስተባባሪነት በተዘጋጀው የ2016 ዓ.ም የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ የዩኒቨርስቲው ሁሉም ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የስራ ሀላፊወች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ተማሪወችና ማህበረሰብ በተገኙበት የኢድ አልፈጥርን በአል በጋራ አክብረዋል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን የ1445ኛውን የኢድ አልፈጥር በአል ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ከተማሪወቻቸው ጋር የበአሉ ተካፋይ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ለእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪወች፣ መምህራን እና ሰራተኞች፤ ለደብረ ታቦር ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ፣ እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለው እንደገለፁት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አመታዊ በአላትን ከተማሪወች ጋር በጋራ ማክበር ቤተሰባዊነትን የሚያጎለብት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰው የሮመዳን የፆም ወር አልቆ ለኢድ አልፈጥር በአል በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀው ይህ ዝግጅትም ተማሪወች በዓልን ከቤተሰብ ጋር አብረው እንዳሳለፉ እንዲሰማቸው ያደርጋል በማለት ለበአሉ አዘጋጆች እና ለተሳታፊወች በሙሉ ምስጋና አቅርበው፤ ልክ እንደ ኢድ ሁሉ ከአብይ ፆም በኋላ ደግሞ ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የዩኒቨርሲቲው እስልምና እምነት ተከታይ ተማሪወችን በመወከል መልክት ያስተላለፈው ተማሪ ሰዒድ እንደገለፀው በታላቁ ወር ሮመዳን ፃም ፀሎትን፣ ፍቅርና አንድነትን፣ ትብብርና አብሮነትን፣ ትህትናና ሰላምን መርህ በማድረግ እንዲሁም ለተቸገሩ የመድረስ እና የይቅርታና እና የፍቅርን አስተምርሆ ነብያችን ያስተማሩን በመሆኑ የህይወታችን መመሪያ ልናደርገው ይገባል በማለት ለመላው ሙስሊም ተማሪወችና ማህበረሰብ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ በማለት መልክቱን አስተላልፏል። በተጨማሪም
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንቶች፣ ሰራተኞች እና ተማሪወች እረፍታቸውን በመተው በዓሉን በዚህ መልኩ በጋራ እንድናከብር ስላስቻሉን ደስታችን ከፍ ያለ ነው በማለት ምስጋና አቅርቧል።