
ማስታወቂያ:- ለደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 28 እስከ 30/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ጥሪ ተላልፎ የነበረ ቢሆንም፤ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት ቅበላና ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እየገለጸ፤ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደተጠናቀቁ በድጋሜ ጥሪ የሚተላለፍ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት