
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 1446ኛውን የኢድ-አል ፈጥር በዓል በድምቀት አከበረ ።
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 1446ኛውን የኢድ-አልፈጥር በዓልን የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት አክብሯል ።
በበዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ እረዳት አቶ ይሁን አያሌው
ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለአንድ ወር ያህል በትጋት ሲያከናውኑት የነበረውን የፆም ጊዜ ጨርሰው በዓላቸውን የሚያከብሩበት የደስታ ወቅት ነው:: በዚህም የደስታ በዓል ላይ ወዳጅ ከወዳጁ ይጠያየቃል ፤ የተራቡና የታረዙ ወገኖች ይጎበኛሉ፤ ሁሉም ያለውን ያካፍላል፤ ደስታ በሁሉም ቤት ይገባል:: ዛሬ እየተከበረ ያለው 1446ኛውን የኢድ በዓል እነዚህ እሴቶች ተጠብቀው በድምቀት እየተከበረ በመሆኑ ደስታዬ ልዩ ነው እንኳን አደረሳችሁ ኢድ ሙባረክ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ሀብታሙ ሲሳይ በጾሙ ወር የነበራችሁን አብሮነት እና መረዳት ከዚህ በኋላ በትህምርት ቆይታችሁ በሀሉም መስክ መደጋገፉን አጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ነጋሽ ትምህርት እና እምነተ የማይነጣጠሉ እና ሁለቱን አጣምረው በሚዛኑ ያስኬዱ የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸው ተማሪዎቹም ይህንን ፈለግ ተከትለው እንዲሄዱ አሳስበው በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።







