የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በድምቀት አስመረቀ፡፡
ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ፤ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቅድመ እና በድኅረ-ምረቃ መርሀግብሮች ያስተማራቸውን 544 ተማሪዎችን በድምቀት ያስመረቀ ሲሆን ዩኒቨርስቲው ለ11ኛ ዙር ለምረቃ ካበቃቸው ተማሪዎች መካከል 403 ወንዶች ሲሆኑ 141 ደግሞ ሴቶች ናቸው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው ተመራቂዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠው የመውጫ ፈተና ከ92 % በላይ በማምጣት ዩኒቨርሲቲያችን ከቀዳሚዎች ተርታ መሰለፉን ያሳያል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አክለውም በተመራቂዎቻችን ሁለንተናዊ ስኬት የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የበለጠ ይታወቅ ዘንድ በዓላማችሁ ፀንታችሁ እና የሙያ ስነ-ምግባር ተላብሳችሁ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እና ሀገራችሁን በቁርጠኝነት እንድታገለግሉ ሲሉ መልዕክት ስተላለፉ ሲሆን
ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ላይ በአለው ከፍተኛ ትኩረት ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ እንዲችል አጋዥ ኘሮጀክቶችን ለይቶ ቅድሚያ በመስጠት በተለይ ለICT መሰረተ ልማት ግንባታ የአደረግገው ከፍተኛ ርብርብ የኢንተርኔት፣ የዲጅታል ቤተመፃህፍት ወዘተ… አገልግሎት አሰጣጥን የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት የሚያስችል ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ዩኒቨርስቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ዋጋቸው 800000 ብር የሆነ 23696 መጽሀፈትን ከBook for Africa ለ 37 ትምህርት ቤቶች ያተሰራጨ ሲሆን፤
በከተማው ጸጉር ሚካኤል ቀበሌ ግምቱ 80060 ሽህ ብር የሚያወጣ ሰባት የውሃ ጉድጓድ ጥገና የተከናወነ ሲሆን ይኸም የአካባቢውን ማህበረሰብ የውሃ ችግር መቅረፍ እንዳስቻለ ገልጸዋል፡፡
የደብረ ታቦር ዩኒሸርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው በመጨረሻም የደብረ ታቦር ከተማ ማህበረሰብ ምንም እንኳን ለልጆቹ ላደረገው ነገር ምስጋና መቀበልን ጠብቆ ባያደርግም ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጣችሁትን ልጆቹን ከልጆቹ ሳይለይ ከመጀመሪያ ቀን እግራችሁ ከተማዋን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ላደረገላችሁ ፍቅር ለበዛበት እንክብካቤ እናንተን ውድ ተመራቂ ተማሪዎች እና ወላጆቻችሁን ወክየ ማመስገን እወደለሁ ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በመጨረሻም በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠው የመውጫ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች እና በትምህርት ክፍላቸው እና በዩኒቨርስቲው ደረጃ አብላጫ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች የሰረተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት በዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ፣ ምርምርና ማህበረሰብ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንበሩ ተሾመ አቅራቢነት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው እና ከአስተዳደርና ልማት ም/ ፕሬዚዳንት ተወካይ ከዶ/ር የሽዋስ መብራት እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡