የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ማዕከል ከ”ብራይተር ጀነሬሽን” (Brighter Generation) ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ከደብረ ታቦር ከተማ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተዉጣጡ ተማሪዎችን አስመረቀ
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ እና ምርምር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንበሩ ተሾመ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው ለዛሬ ተመራቂዎች በትምህርት ህይወታቸው ስኬታማነት ላይ የጎላ አስተዋጽዖ እንዳለው በመግለጽ ተማሪዎቹ ያገኙትን ክህሎት ለሌሎች በማካፈል ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሳድጉት አደራ ብለዋል።
ም/ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ስልጠና እንዲሰጥ ድጋፍ ላደረገው “Brighte Generation” አለም አቀፍ ድርጅት እና ለአሰልጣኞች በሙሉ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ስም ምስጋና በማቅረብ ለተመራቂ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
በበይነ መረብ በተሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ 9 ሴት እና 14 ወንድ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኞቹ ባለፉት የክረምት ወራት በ Leadership, communiation skills,Critical Thinking and Community Development Project ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎችን በአግባቡ ተከታትለው ማጠናቀቃቸው አዳዲስ እውቀቶችን እንዳገኙ የገለጹ ሲሆን ይኸም በቀጣይ የትምህረት ህይወታቸው ለተሻለ ስኬት እንደሚያበቃቸው ገልጸዋል ፡፡