ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
- Categories Uncategorized, አማርኛ ዜና
- Date September 25, 2024
በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ምዝገባ መስከረም 28-30/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በ2016 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች መምጣት ያልቻለችሁ እና ዊዝድሮዋል መሙላት ሳትችሉ የቀራችሁ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን ከቀጣይ ባች ጋር መቀጠል እንድትችሉ ዩንቨርስቲው ስለፈቀደ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ አመት የምትቀላቀሉ (2016 ዓ.ም ሪሚዲያል የነበራችሁና በአዲስ የምትመደቡ) ተማሪዎች ደግሞ በሌላ ማስታዎቂያ ጥሪ ስለምናስተላልፍ በትዕግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
• ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መግባት አይቻልም፡፡
• ለበለጠ መረጃ የዩንቨርሲቲውን ድህረገጽ www.dtu.edu.et ን ይጎብኙ፡፡
ደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት